
በዞኑ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ የነበሩት ኢ/ር በለው ሀብታሙ ነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የከተማውን የፀጥታ ሁኔታ በማስከበር በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ በተተኮሰ ጥይት ተመተው በተወለዱ በ33 አመታቸው ህይወታቸው አልፏል።
ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ በክትትል ላይ ይገኛል።
ከክልሉ ፖሊስ መምሪያ ባገኘነው መረጃ ኢ/ር በለው ሀብታሙ ባለትዳርና የ1 ሴት ልጅ አባት ነበሩ።
ሚኪያስ ፀጋዬ