መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 19፣2012-ተጠግነው አገልግሎት የሚሰጡ ንብረቶችን በመለየት ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየተከናወነ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን ከማስወገድ በተጓጋኝ ተጠግነው አገልግሎት የሚሰጡትን ንብረቶች በመለየት ወደ ስራ የማስገባት ስራ እያከናወነ መሆኑን የተቋሙ ንብረት አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ዳዲ እንደገለፁት ንብረቱ ተጠግኖ የሚሰጠውን አገልግሎትና የጥገና ወጪውን ከግምት ውስጥ ለማስገባት በየስራ ክፍሉ የልየታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡

በተቋሙ የንብረት አያያዝና አስተዳደር ላይ የሚስተዋለውን ክፍተት ለመሙላትም በቴክኖሎጂ የታገዘ የንብረት ማደራጀት ስራ መጀመሩንም ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡

ንብረቶችን ለማደራጀት እና ለማስተዳደር የንብረት ዋጋ ክለሳ እና ወቅቱ የሚጠይቀውን የተቋም ሀብት ዕቅድ ስርዓት (Enterprise Resource planning system) የመዘርጋት ስራ በመሰራት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *