መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 20-2012-በአሜሪካ የሪፐብሊካን ጉባኤ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ሚላኒ ትራምፕ በዘር መከፋፈል አያስፈልግም ለአንድነት እንስራበት ስትል ተናግራለች

አላስፈላጊ የሆኑ ሃሳቦችን ከዘር ልዩነት ጋር በተያያዘ ማሰብ እንዲሁም በአሜሪካ ታሪክ ዙሪያ ሚዛናዊ ሆኖ ነገሮችን መመልከት ተገቢ ነው ስትል ሚላኒ ትራምፕ ገልፃለች፡፡
በሪፐብሊካኑ ጉባኤ ማብቂያ ላይ በነገው እለት ዶናልድ ትራምፕ መልዕክታቸውን እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል፡፡
ሰኞ ምሽት በመጀመሪያው እለት የሪፐብሊካኑ ጉባኤ 17 ሚሊየን ሰዎች የተከታተሉት ሲሆን የዲሞክራቶችን የመክፈቻ እለት ጉባኤ 19.7 ሚሊየን ሰዎች በመከታተል ብልጫ አግኝቷል፡፡
ሚላኒ ትራምፕ ስለ ባለቤቷ ትራምፕ ስትናገር እርሱ የሚመሰገን ሰው ነው የሚሰማውን ሁሉ ያለ አንዳች ሚስጥር ይፋ ያደርጋል ስትል ተናግራለች፡፡
ለአሜሪካውያኑ የሚገባ በአጠቃላይ ታማኝ ሰው ነው ስትል ተደምጣለች፡፡ አሉታዊ እና የሀሰት የሆኑ ጥቃቶች ከሚዲያዎች ቢሰነዘርበትም ትራምፕን አላስቆሙትም ስትል ሚላኒ ትራምፕ ተናግራለች፡፡
እርሱ ሀገሩን ይወዳል እንዴት መስራት እንዳለበትም ያውቃል ስትል ሚላኒ ትራምፕ አሣውቃለች፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *