መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 20-2012-ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት አዳዲስ የቴሌኮም አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት አዳዲስ የቴሌኮም አገልግሎቶችን በዓመታዊው ሪፖርቱ ላይ ይፋ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቱ በነባር አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን ኢትዮ ቴል የሞባይል መተግበሪያ፣ ኢትዮ ቢኬር ወይም ፖርታል መልካም ማለዳ፣ አደይ አበባ የሞባይል ጥቅል ተቋሙ ይፋ ካደረጋቸው መካከል ናቸው።

ከዚህ ቀደም በቤትዎ ይቆዩ በሚል ይፋ ያደረገው አገልግሎት ላይ 59 በመቶ ቅናሽ በማድረግ በጤናዎ ይቆዩ በሚል ማቅረቡ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ የ3 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እንዲሁም የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድን አቅጣጫ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ይፋ አድርገዋል።

በዚህም በድምፅ ጥቅል አገልግሎት ላይ የ29 በመቶ ቅናሽና በኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት ላይ 35 በመቶ እንደተደረገ ጠቅሰዋል።

የፕሪሚየም ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል አገልግሎት 21 በመቶ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን በሞባይል የድምጽ እና ዳታ ጥምር አገልግሎት ላይ 28 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።

የሳተላይት አገልግሎት ላይም 61 በመቶ ቅናሽ ሲደረግ በፕሪሚየም ፕላስ ያልተገደበ የጥቅል አገልግሎት ላይ ደግሞ 16 በመቶ ቅናሽ ነው የተደረገው።

ፕሪሚየም ያልተገደበ የድምጽ እና ዳታ ጥቅል አገልግሎት 20 በመቶ ቅናሽ ሲደረግም የፕሪሚየም ያልተገደበ የዳታ ጥቅል አገልግሎት 21በመቶ ተደርጓል።

ድርጅቱ በአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት አደይ አበባ ጥቅል አገልግሎት በሚል 53በመቶ ብሎም ለዓለም አቀፍ አየር ሰዓት አገልግሎት 100በመቶ የአየር ስጦታ ለደንበኞች እንደሚያቀርብ ይፋ አድርጓል። በተያዘው በጀት ዓመት55 ነጥብ5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ኢቢሲ ዘግቧል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *