መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 20-2012-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከድምጻዊ ሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ሁከት በኦሮሚያ ክልል 67 ምዕመናን እንደተገደሉባት አስታወቀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጠረው ሁከት ምክንያት ተጎድተዋል ወደ ተባሉ አካባቢዎች ተሰማርታ ምልከታ ካካሄደች በኋላ በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት መግለጫ በመሰጠት ላይ ትገኛለች።
ቤተክርስቲያኗ በዚህ ጊዜ እንዳለችው ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ገድያ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረ ሁከት 67 ምዕመናን ሲገደሉ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።
በአጠቀላይም ሁከቱን መነሻ በማድረግ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምዕመናን ንብረት መውደሙም በመግለጫው ላይ ተገልጿል።
በኦሮሚያ ክልል፣በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር እና በሌሎች አካባቢዎች ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ እንደ ሰውም አስክሬናቸው በክብር አልተቀበረም ፣ ሴቶች በባለቤታቸው፣በወንድምና በአባታቸው ፊት መደፈራቸው በምልከታ መረጋገጡ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *