መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 22-2012-ሀሪኬን ላውራ የተሰኘው ወጀብና ከባድ አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ መሆኑ ተሰማ

በአሜሪካ ሉዚኒያ ግዛት በሀሪኬን ላውራ የተነሳ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ያጋጠመ ሲሆን በርካታ መኖሪያ ቤቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።
ከግማሽ ሚሊየን በላይ መኖሪያ ቤቶች የሀይል አቅርቦት እንዲቋረጥባቸው አስገድዷል።ይህ ሀሪኬን ላውራ የተሰኘው ከባድ ወጀብ በሰዓት 240 ከ.ሜ ንፋስ እንዳስከተለም ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እያመለከቱ ይገኛል።
የአደጋና የድንገተኛ ባለሙያዎች በቴክሳስና ሉዚኒያ የሚገኙ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቴክሳስና የሉዚኒያ ግዛት ገዢዎችና ባለስልጣናት የሚያስተላልፉትን መመሪያ ዜጎች እንዲተገብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በዚሁ ወጀብና አውሎ ንፋስ ክፉኛ በተጎዱት ሀይቲና ዶምኒክ ሪፐብሊክ የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል።በኩባና ጃማይካ ላይ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት አውታር ላይ ውድመት አስከትሏል።
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *