መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 22-2012-መፈንቅለ መንግስት የተፈፀመባቸው የማሊ ፕሬዝዳንት ከእስር ተለቀቁ

መፈንቅለ መንግስቱን ያቀነባበሩ ሀይሎች በትላንትናው እለት የማሊ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኬታን ከእስር ለቀዋል።በቀጠናው ሀገራት የተመራው ውይይት ለማሊ ቀጣይ የፖለቲካ ጉዞ ተስፋን የሚሰጥ ስለመሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል።
ኬታ ከስር የተለቀቁት ከዘጠኝ ቀናት ቆይታ በኃላ ሲሆን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ማቅናታቸው ታውቋል።በሀገሪቱ የጂሃዲስቶች ጥቃት በሳህል ቀጠና መስፋፋቱን ተከትሎ ብሎም በሙስና ቀውስ የተነሳ ኬታ ከስልጣን እንዲወርዱ ግፊት ሲደረግ ቆይቷል።
ኬታን በሀይል ያስወረደው የጦሩ ሀይል የባማኮን ቤተመንግስት በመልቀቅ ወደ ካምፕ እንዲመለስ በዓለም አቀፍ መንግስታት ዘንድ ጥሪ እየቀረበ ይገኛል።የሽግግር መንግስት ለመመስረት በጦሩ የሚመራው መንግስት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *