መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 22-2012-ሱዳን በታሪኳ ከፍተኛ የተባለ የጎርፍ አደጋ እያስተናገደች ትገኛለች

በሱዳን ከፍተኛ መጠን ያለው ጎርፍ መከሰቱን ተከትሎ ከ86 በላይ ሰዎችን ህይወት ሲነጥቅ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች በመዲናዋ ካርቱም ጨምሮ ወድመዋል።
በክረምት ወራት በሱዳን ምንም እንኳን ጎርፍ መከሰቱ የተለመደ ቢሆንም በመዲናዋ ካርቱም ዋና አውራ ጎዳና ላይ በመንገድ በመዝጋት ከፍተኛ ጥፋት ሲያስከትል የአሁኑ የመጀመሪያው ሆኗል።
የሱዳን የመስኖ ሚንስትር ያስር አባስ በትላንትናው እለት እንደተናገሩት የብሉ ናይል አማካይ ከፍታ 17.43 ሜትር መድረሱን ይፋ አድርገዋል።ይህም ሱዳን የናይልን የውሃ መጠን ከፍታ መመዝገብ ከጀመረችበት እ.ኤ.አ ከ1912 ወዲህ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝገቧል።
በካርቱም ሆነ የካርቱም መንትያ ከተማ በሆነችው ኦምዱርማን እንዲህ አይነቱ ከፍተኛ ጥፋት ያስከተሎ ጎርፍ እስካሁን ባይመዘገብም ቀጣይነት እንዳለው የሱዳን የጎርፍ አደጋ ሚንስቴር ይፋ አድርጓል።
ኢትዮጲያ እየገነባችው የምትገኘው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለሱዳን ጎርፍን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *