መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 22-2012-በላይቤሪያ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት የሚደርስባቸው ዜጎች ቁጥር መጨመር ፕሬዝዳንት ዊሃን ጫና ውስጥ መክተቱ ተሰማ

የጾታዊ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎችን መከላከል አልቻሉም በሚል በጆርጅ ዊሃ አስተዳደር ላይ ጫና የሚፈጥር የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ለዘመቻው መነሻ ከወርሃ ጥር አንስቶ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከ1000 በላይ የጥቃት ሰለባዎች ሪፖርት መደረጋቸውን ተከትሎ ነው።
ላለፉት ሶስት ቀናት በተከታታይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመዲናዋ ሞኖሮቪያ ተቃውሞአቸውን ለመግለፅ አደባባይ ቢወጡም ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ግን በጉዳዩ ላይ ዝምታን መርጠዋል።
በዚሁ ዙርያ የማህበራዊ አንቂ ባለሙያዎች ወሲባዊ ጥቃት በወንጀል መቅጫው ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።
በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *