መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 22-2012- የብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች

~ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ባጋጠማቸዉ ከፍተኛ ህመም የተነሳ ስልጣናቸዉን ሊለቁ እንደሚችል ተነገረ፡፡የ65 ዓመቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዛሬ ከሰዓት በጤናቸዉ ዙርያ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በህመማቸዉ ዙርያ ግልጽ የሆነ መረጃ አልተሰጠም፡፡
~ በሪፓብሊካዉያኑ ጉባዔ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት ዶናልድ ትራምፕ የቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ተፎካካሪያቸዉ ጆ ባይደን በምርጫዉ ቢያሸንፉ አሜሪካን ሊያፈራርሱ ይችላል ሲሉ ተናገሩ፡፡ዲሞክራቶች ጸብ ጫሪ ናቸዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
~ የዩጋንዳዉ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ነገ ቅዳሜ ነሀሴ 23 በመላዉ ሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ዙርያ የጸሎት መርሃ ግብር እንደሚከናወን አስታወቁ፡፡
~ በኒጀር መዲና ኒያሚ ያጋጠመዉ የጎርፍ አደጋ ከ250 ሺ በላይ ሰዎችን ከመኖሪያ ቤታቸዉ ሲያፈናቅል የ45 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
~ በህንድ በ24 ሰዓት ዉስጥ 77,266 በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ሪፖርት ተደረገ፡፡በመላዉ ሀገሪቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች 3.3 ሚሊየን ሲደርስ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 61,529 መድረሱ ሪፖርት ተደርጓል፡፡

~ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር 180,527 ሲደርስ የቫይረሱ ተጠቂዎች 5.8 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡
~ በእርስ በእርስ ቀዉስ ዉስጥ በምትገኛዉ ሶርያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *