መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 25፣2012-በቤሩት ያጋጠመውን ፍንዳታ ተከትሎ ሙስጠፋ አዲብ ቀጣዩ የሀገሪቱ ጠ/ሚ ሊሆኑ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል

በጀርመን የሊባኖስ አምባሳደር የሆኑት ሙስጠፋ አዲብ ከፍተኛ ድጋፍ ከፖለቲከኞች እያገኙ ይገኛል፡፡
በቤሩት ያጋጠመውን ፍንዳታ ባስከተለው ህዝባዊ ቁጣ በሀሰን ዲአብ የሚመራው መንግስት ከስልጣን እንዲወርድ አስገድዷል፡፡
ከ 2013 አንስቶ በጀርመን የሊባኖስ አምባሳደር በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት የ 48ዓመቱ አዲብ በፈረንሳይ እና ሊባኖስ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በፖለቲካል ሣይንስና ህግ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡
የቀድሞ የሊባኖስ ጠ/ሚ ናጂብ ሚካቲ አማካሪ በመሆንም ሰርተዋል፡፡ ተጨማሪ ተፎካካሪ ካላገኙ አዲብ የሀገሪቱ ጠ/ሚ ይሆናሉ፡፡
በቤሩት ባጋጠመው የአሙኒየም ናይትሬት ፍንዳታ ቢያንስ የ 200 ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፡፡
በዛሬው እለት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ሊባኖስ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *