መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 25፣2012-በኦሪጎን ፖርትላንድ በጎዳና ላይ ያጋጠመውን ግጭት ተከትሎ ትራምፕ እና ባይደን የቃላት ጦርነት ውስጥ መግባታቸው ተሰማ

በፖርትላድ ከተማ ያጋጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ባስከተለው ግጭት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የከተማዋ ከንቲባ ዲሞክራቱ ቴድ ተጠያቂ በማድረግ ሃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል ብለዋል፡፡
ዲሞክራቱ ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን በበኩላቸው ግዴለሽ ግጭትን የሚያበረታቱ ሲሉ ትራምፕን ወቅሰዋል፡፡
በፖርትላንድ ባሣለፍነው ቅዳሜ የትራምፕ ደጋፊዎች ድጋፍ ለመስጠት አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ ከብላክ ላይቭስ ማተር ተቀናቃኞች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በተተኮሰ ጥይት የአንድ ሰው ህይወት አልፏል፡፡
አፍሪካዊው አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በሚኒያ ፖሊስ ከተገደለ በኋላ በፀጥታ አካላት እና ዘረኝነት በሚያወግዙት መካከል ከፍተኛ ግጭት ሲከሰት ተስተውሏል፡፡
ትራምፕ ፖርትላንድ በማይረባ ከንቲባ እየተመራች መቼም ብትሆን ከዚህ ዓይነት ሁኔታ አታገግምም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩን ለማስተካከል ባይደን ፍቃደኛ አልሆኑም ብለዋል፡፡ በከተማዋ ያጋጠመውን ግጭት ተከትሎ 10 ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *