መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 25፣2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ በጃፓን ከህዝብ በተሰበሰበ ድምፅ መሰረት የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ሺጉሩ ኢሺባ ቀጣዩ የጃፓን ጠ/ሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ የጃፓን ጠ/ሚ ሺንዞ አቤ ለዓመታት ለህመም ሲዳርጋቸው በነበር የጤና እክል የተነሳ ከስልጣን መልቀቃቸው ይሰማል፡፡
~ በሜክሲኮ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ 64ሺህ በለጠ፡፡ በቫይረሱ በሀገሪቱ የ 64‚158 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 595 ሺ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡
~ በብራዚል በ 24ሰዓታት ውስጥ 566 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በአጠቃላይ በብራዚል የሟቾች ቁጥር ከ 120ሺህ ልቋል፡፡
~ የካናዳ የመጀመሪያ ጠ/ሚ ሰር ጆን ማክዶናልድ ሀውልት በሞትሪያል የሚገኝ ሲሆን በተቃዋሚዎች የተነሳ እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ የዘር መድሎና የፖሊስ የሃይል እርምጃ ዜጎችን አስቆጥቷል፡፡
~ የቼክ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሚሎስ ቫስትርሲል በታይዋን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ቻይና አፈጉባኤው ለድርጊታቸው ከባድ ቅጣት ይከፍላሉ ብለዋል፡፡ ቻይና ከታይዋን ጋር የሚደረግ የሁለትዮሽ ግንኙነትን በመቃወም ታይዋን ግዛቴ ናት ትላለች፡፡
~ በደቡባዊ ጣሊያን የባህር ዳርቻ 20 ስደተኞችን አሳፍራ በነበረች ጀልባ ላይ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ የ 3 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ተጨማሪ 5ሰዎች ክፉኛ ተጎድተዋል፡፡
~ የቤላሩስ ፕሬዝደንት ልደት በማስመልከት ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ የሚኒስክ ከተማ ዜጎች መልካም ልደት እርሶ አይጥ ኖት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለ 26ዓመታት ቤላሩስን የመሩት ሉካሼንኮ ከስልጣኝ እንዲወርዱ የሚደረግባቸውን ግፊት ተከትሎ ተቃዋሚዎቻቸውን አይጦች ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *