መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ ነሐሴ 28፤2012-በደቡብ ኦሞ ዞን በተከሰተው ጎርፍ የ4 ሰው ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

በደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ ከሐምሌ 25 ጀምሮ የተከሰተው የኦሞ ወንዝ ሙላት ባስከተለው ጎርፍ በውሃ የተከበቡ 19 ደሴቶች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን ለማውጣት በሞተር ጀልባ የታገዘ ጥረት በማድረግ 43,670 ቤተሰቦችን ማውጣትና በ8 ደረቃማ አከባቢዎች ማስፈር መቻሉን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ናጎሊዮ አስታውቀዋል።
በክልሉ መንግሥት በዳሰነች በጎርፍ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን አውስተው እየተደረገ ያለው የእለት ቀለብ አቅርቦት ከተፈናቃዮች ቁጥር ጋር ተመጣጣኝ አይደለም እስካሁን የቀረበ ያለው የ15 ,982 ሰዎች ቀለብ ሲሆን ቀሪ 27,688 ሰዎች ቀለብ ባለመቅረቡ መቸገራቸውን የወረዳው ም/አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ገልፀዋል፡፡
ጎርፉ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት በማድረስ ከደሴቱ እየወጡ በነበሩ ጊዜ ጀልባው በመገልበጡ 1 ህፃን 2 ሴቶች እና 1 አዛውንት አርብቶ አደሮች በድምር የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል።
ጎርፉ በእንስሳትና እርሻ መሬት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷልም ብለዋል።አቶ ታደለ እንዳሉት በወረዳው በጎርፍ የተፈናቀሉ ሰዎችን ያሰፈርንበት አከባቢዎች ዳግም በጎርፍ በመከበባቸው የሰብዓዊ ድጋፍ የማድረግ ስራችንን አዳጋች አድርጎታል በ ኮሮ ፡ ሲኤስ፡ ዶሼ እና ደሜች ቀበልያ መንገድ መቋረጡን ገልፀዋል፡፡ጎርፉ ከባድ በመሆኑ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በውሃ የተከበቡ ነዋሪዎችን በማውጣት በሌላ አካባቢ ለማስፈር በሄሊኮፕተር የታገዘ ጥረት መደረግ እንዳለበት መግለፃቸውን ከዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *