መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 28፤2012-በድሬዳዋ ከተማ የካናቢስ ዕፅ በአንድ ባጃጅ ላይ በመጓጓዝ ላይ እንዳለ በቁጥጥር ስር ውሏል

አደንዛዥ እፁ ሊያዝ የቻለው በትላንትናው እለት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ በድሬዳዋ ከተማ በ09 ቀበሌ በተለምዶ ስሙ አሸዋ ደርዘን ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ነው።
በአንድ ማዳበሪያ ሙሉ እና በኩርቱ ፌስታል አደገኛ የካናቢስ ዕፅ ተሞልቶ በአንድ ባጃጅ ላይ በመሄድ ላይ እንዳለ የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትአባላት ባደረጉት ክትትል የባጃጅ አሽከርካሪው ከአደገኛ ካናቢስ ዕፁ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በቁጥጥር ሥር ያዋሉትን ተጠርጣሪ ግለሰብ የፍርድ ቤት መበርበሪያ ፍቃድ በማውጣት ተጨማሪ ሁለት ግማሽ ግማሽ ማዳበሪያና ሌላ 200 ሊትር በሚይዝ ጀረካን ውስጥ ሙሉ የአደገኛ የካናቢስ ዕፅ በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡
ፖሊስ በአሁን ወቅት በጉዳዩ ላይ ተያይዞ 5 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የምርመራ ሂደቱም እየተጣራ እንደሚገኝ የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን የለውጥ ሥራዎች ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *