መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 29፤2012-በሞተር ሳይክል በመንቀሳቀስ ጥቃት የፈጸሙ ታጣቂዎች 22 ሰዎችን መግደላቸዉ ተሰማ


በናይጄሪያ ማዕከላዊ ግዛት በሆነችዉ ኒጀር ሞተር ሳይክልን በመጠቀመ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የ22 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡በጥቃቱ ህይወታቸዉን ካጡት መካከል የጸጥታ አካለት እንዳሉበት ተነግሯል፡፡
ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ለመፈጸም ያሴሩት ወደ መኖሪያ መንደር በመግባት ሰዎችን ለማገት እንደነበር ኮለኔል ካቢሩ ማኩንዲ ተናግረዋል፡፡በግዛቲቱ የተለያዩ የወንጀል ቡድኖች መሰል ጥቃትን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየፈጸሙ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይ ባሳለፍነዉ እሮብ በአካባቢዉ በምትገኝ ካጋር በተባለች ከተማ ሞተር ሳይክልን በመጠቀም የታጠቁ ሀይሎች ባንክ ለመዝረፍ በነበረ ጥቃት 3 የጸጥታ አካላትና ንጹሃን ተገድለዋል፡፡
በአካባቢዉ ያለዉን የጸጥታ መደፍረስና የተደራጁ የወንጀል ቡድኖችን እንቅሰቃሴ ከጸጥታ አካላት ቁጥጥር ዉጪ እየሆነ ይገኛል፡፡
በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *