መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 29፤2012-አፍሪካ 220 ሚሊየን ዶዝ ክትባት እንደምታገኝ የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ


የአለም የጤና ድርጅት ይፋ እንዳደረገዉ ከሆነ የተረጋገጠ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ከተገኘበት ጊዜ አንስቶ የመጀመሪያ ዙር ቢያንስ 220 ሚሊየን ክትባት አፍሪካ እንደምታገኝ አስታዉቋል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ መርሃ ግብር ዋና ሀላፊ ሪቻርድ ሚሂጎ የመጀመሪያ ዙር የክትባት መድሃኒት ተደራሽ የሚሆነዉ ለጤና ባለሙያዎችና ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እንደሆኑ አስታዉቀዋል፡፡
የ1.3 ቢሊየን ህዝቦች መኖሪያ በሆነችዉ አፍሪካ የአህጉሩ 54 ሀገራት የክትባት መድሃኒቱን ለማግኘት ፍላጎት ማሳየታቸዉን ሪቻርድ ሚሂጎ ተናግረዋል፡፡
በኮቫኤክስ ዓለም አቀፍ የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒት ምርምር ጥምረት 2 ቢሊየን ዶዝ መድሃኒት ለመግዛት ዉሳኔ ላይ የተደረሰ ሲሆን ዘጠኝ መድሃኒቶች በእጩነት ተመርጠዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *