መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 29፤2012-የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለነገ የጠራው አስቸኳይ ስብሰባ አጀንዳው ካልተነገራቸው የትግራይ ተወካዮች እንደማይሳተፉ የክልሉ ም/ቤት አስታወቀ!


የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አስቻኳይ ስብሰባ ነሐሴ 30/2ዐ12 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እንደሚካሔድ መግለጹ ይታወቃል፡፡ለስብሰባው የም/ቤቱ አባላት ነሐሴ 29 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም በፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉም አስታውቋል፡፡
ይሁንና የስብሰባው አጀንዳ ካልታወቀ የትግራይ ክልል ተወካዮች እንደማይገኙ የክልሉ ም/ቤት ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ ማሳወቁን የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በፌስ ቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡በፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልሉ ተወካዮች አጀንዳውን አውቀው ሳይዘጋጁ መሳተፍ እንደማይችሉ ነው በደብዳቤው ላይ የተገለጸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *