መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 2፤2012 -የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ለዶናልድ ትራምፕ ባስተላለፉት መልዕክት በፍልስጤም ጉዳይ ፍትሃዊ የሆነ መፍትሄ ላይ መድረስ እንፈልጋለን ሲሉ ይፋ አድርገዋል

የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ትራምፕ ጋር በነበራቸው የትላንትናው የስልክ ቆይታ በአረቡ አለም ሰላም እንዲሰፍን የሚደረገው ጥረት ፍትሃዊና ዘላቂ መፍትሄ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡
አሜሪካ በእስራኤልና በተባበሩት አረብ ኤምሬት መካከል ለመጣው ሰላም ያደረገችውን ጥረት ንጉስ ሰልማን በማድነቅ ይኸው ሰላም ፍልስጤም ደጅ እንዲደርስ ጠይቀዋል፡፡
ግብፅ፣ዮርዳኖስና ከእስራኤል ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ያሻሻሉ ሀገራት የነበሩ ሲሆን ኤምሬት ተጨምራለች፡፡የትራምፕ አማካሪና የሴት ልጃቸው ባለቤት ጃሬድ ኩሽነር የሰላም ሂደቱን በርካታ ሀገራት ይቀላቀላሉ ሲሉ መናገሩ ይታወሳል፡፡


በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *