መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 3፤2012-እርቃናቸውን አደባባይ የወጡ ሰልፈኖች ፍትህ ለዳንኤል ፕሩድ ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል

ዳንኤል ፕሩድ የተባለ ግለሰብ በኒውዮርክ በጎዳና ላይ እርቃኑን ከነበሩ በኃላ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ ፍትህ ይሰጥ ሲሉ አደባባይ የወጡ ዜጎች ድምጻቸዉን አሰምተዋል፡፡በሮችስተር የፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ዳንኤል ፕሩድ ለምን ተገደለ ሲሉ እርቃናቸዉን በዝምታ በመቀመጥ ተቃዉመዋል፡፡

የ41 ዓመቱ ዳንኤል ፕሩድ ጥቁር አሜሪካዊ ሲሆን እርቃኑን በጎዳና ላይ ሲሮጥ ያስቆሙት የፀጥታ አካላት እንቅስቃሴዉን እንዲገታ መላዉ ፊቱን የሚሸፍን ጭንብል በሀይል አድርገዉበታል፡፡ለሁለት ደቂቃ መተንፈስ ያልቻለ ሲሆን ወደ ህክምና ተቋም ካመራ ከአንድ ሳምንት በኃላ ህይወቱ አልፏል፡፡

ወንድሙ ጆኢ ፕሩድ ሲናገሩ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአእምሮ ጤናዉ እየታወከ መምጣቱን ገልጿል፡፡የፖሊስ አባላት በግለሰቡ ላይ እንዲህ ዓይነት ድርጊት ሲፈጽሙ የሚያሳየዉ ምስል መለቀቁ ቁጣን ፈጥሯል፡፡ተቃዋሚዎች ድርጊቱን የፈጸሙ የፖሊስ አባላት ተጠያቂ እንዲሆን እየጠየቁ ይገኛል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *