መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 4፤2012የፍቅር አጋሮን ውሃ አጣጮም የት ያገኙ ይሆን?


በህንድ ፓርዲሽ ግዛት ነዋሪ የሆኑት ግለሰቦች የተገናኙበት መንገድ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
የ70 ዓመቱ ሲንግህ ባጋጠመው ህመም የተነሳ ወደ ሆስፒታል ያመራል፡፡ ህመሙ ከፍተኛ ስለነበረ አልጋ እንዲይዝ ይገደዳል፡፡
በተመሳሳይ የ55 ዓመቷ ሴት ጉድቡዲዲ በህመም ወደ ሆስፒታል ገብታ አልጋ ትይዛለች፡፡ እነዚሁ ግለሰበች በዚህ አስጨናቂ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዘመን ለሶስት ቀናት በሆስፒታል አንድ ክፍል እንዲተኙ የተደረገ ሲሆን በመካከላቸው ግን ፍቅር ይፈጠራል፡፡
ለሶስት ቀናት በአይን ፍቅር ውስጥ የነበረው ሂደት አድጎ ተሞሽረው ከሆስፒታል መውጣት ችለዋል፡፡
ሲንግህ ከቀድሞ ባለቤቱ የተለያየ ሲሆን አራት ልጆችና 12 የልጅ ልጆች አሉት፡፡ በሆስፒታሉ በራፍ ደማቅ ስነስርዓት እንደነበረ ኢንዲያን ታይምስ ፅፏል፡፡


በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *