መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 4፤2012-የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ቫይረስ ክትባት ላይ የሚያደርገውን ቅድመ ሙከራ አቋረጠ።

ተሰማ በአስትሪዚኔካ እና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተሰራ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒት ሙከራ ስለተደረገባቸው ሰዎች ላይ ምንነቱ ያልተብራራ ህመም ማጋጠሙን ተከትሎ ሂደቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ በአስትሪዚኔካ እና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተሰራ የሚገኘው የክትባት መድሃኒት ሁለት የተሻለ የሙከራ ዘርን በስኬት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ የኦክስፎርድ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሂደት መቋረጥ ሲያጋጥመው የአሁኑ ሁለተኛው ነው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ ምርጫ በፊት የኮሮና ቫይረስ መድሃኒት እንዲገኝ ፍላጎት እያሣዩ ቢሆንም የክትባት መድሃኒት ሂደቱ በፖለቲካ ጫና ውስጥ እንዳይወድቅ ስጋት ፈጥሯል፡፡


በስምኦን ደረጄ

#BisratNews #Oxford_University

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *