መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 5፤2012-ሶማሊላንድ በታይዋን ተወካይ ጽህፈት ቤት መክፈቷ ተሰማ

ራስ ገዝ መስተዳድር በሆነችዉ ታይዋን በሶማሊላንድ ተወካይ ጽህፈት ቤትን መክፈቷን ይፋ አድርጋለች፡፡ሶማሊላንድ እና ታይዋን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸዉ በጋራ እሴት ላይ የተመሰረተ ሲሆን ይህም ዲሞክራሲና ነጻነት ስለመሆኑ በታይዋን የሶማሊላንድ ተወካይ ሞሃመድ ሀጊ ተናግረዋል፡፡

በመዲናዉ ታይፒ ሀጊ ከታይዋን የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆሴፍ ዉ ጋር መክረዋል፡፡ታይዋን ተመሳሳዩን ተወካይ ጽህፈት ቤት በሀምሌ አጋማሽ በሀርጌሳ መክፈቷ ይታወሳል፡፡

ታይዋን እና ሶማሊላንድ የጀመሩት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ተከትሎ እንደ ሀገር ያልተቀበሏቸዉ ደግሞም የራሳችን ግዛት ናቸዉ የሚሉት ቻይናና ሶማሊያ ሂደቱን ተቃዉመዋል፡፡በአፍሪካ ከታይዋን ጋር ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላት ሀገር ኢስዋቲኒ ብቻ ናት፡፡

ሶማሊላንድ ከሶማሊያ ነጻነቷን ያወጀችዉ እ.ኤ.አ በ1991 በነበረዉ የሶማሊያ የእረስ በእርስ ቀዉስ ወቅት ነበረ፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *