መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜ 5፤2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ይደረግ በሚል ዉዝግብ በካናድ በረራ ተሰረዘ፡፡በካናዳ የሚገኘዉ ዌስት ጄት አየር መንገድ የ19 ወር ህጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንድታደርግ ማስገደዱን ተከትሎ በተነሳ ዉዝግብ ከካልጋሪ ወደ ቶሮንቶ የነበረዉ በረራ እንዲሰረዝ ምክንያት ሆኗል፡፡

~ በጋና የልማት ሀላፊ በሚል ማዕረግ የተሰጠዉ ቻይናዊ የተለቀቀዉ ምስል በማህበራዊ ገጽ ትስስር ተጠቃሚዎች ዘንድ ዉዝግብ አስነስቷል፡፡በጋና የልማት ሀላፊ የሚል ማዕረግ የሚሰጣቸዉ ሰዎች በማህበረሰቡ ዉስጥ ለዉጥ ላመጡ ሰዎች ነዉ፡፡ታዲያ ቻይናዊዉን ሰዉ እዉቅና በተሰጠዉ አካባቢ በሸክም ከፍ ማድረጋቸዉ በሁለት ጎራ አወዛግቧል፡፡

~ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በአንድ ሬስቶራንት ዉስጥ በተጠመደ የአጥፍሮ ጠፊ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ፡፡ሰባት ሰዎች በጥቃቱ ክፉኛ የቆሰሉ ሲሆን ለጥቃቱ እስካሁን ድረስ ሀላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርመ አልሻባብ ሊፈጽመዉ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡

~ በካሊፎርኒያ ባጋጠመዉ ሰደድ እሳት የተነሳ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ሰደድ እሳቱ 930ሺ ሄክታር መሬትን እንዳወደመ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

~ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤን የጃፓን መንግስት ቃል አቀባይ ዮሺሃይድ ሱጋ ሊተኳቸዉ እንደሚችሉ በጃፓን ተነባቢ የሆነዉ ጋዜጣ ከመራጮቹ አሰባሰብኩት ባለዉ ድምጽ ይፋ አድርጓል፡፡

~ አሜሪካ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ ከ1000 በላይ የቻይና ዜጎችን ቪዛ ከመስጠት መከልከሏ ተሰማ፡፡በጥናትና ምርምራ ቪዛ ወደ አሜሪካ ለመግባት ከጠየቁት መካከል ከ1ሺ በላይ የሚሆኑ ቪዛ ተከልክለዋል፡፡

~ በሱዳን መንትያ ከተሞች ኦምዱርማን እና ካርቱም ባጋጠመዉ የጎርፍ አደጋ ከ500ሺ በላይ ሰዎች ቤት አልባ መሆናቸዉ ተሰማ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *