መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 4፣2013-በኢትዮጵያ ተጨማሪ 485 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 350 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 9 ሺህ 256 የላቦራቶሪ ምርመራ 485 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 64 ሺህ 786 ደርሷል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 350 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 25 ሺህ 333 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ በመረጋገጡ በአጠቃላይ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 22 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 38 ሺህ 429 ሰዎች መካከል 344ቱ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 147 ሺህ 268 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *