መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 5፤2013-በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያለው የመሪዎች ፖሊሲ ዋንኛ የመከራከሪያ አጀንዳ እንደሚሆን ተነገረ

በአሜሪካ ያጋጠመው ከፍተኛ የሰደድ እሳት አደጋ በቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለሚፎካከሩት ከፍተኛ የልዩነት ነጥብ ሆኗል፡፡

በትላንትናዉ እለት የሰደድ እሳት ክፉኛ በጎዳት የካሊፎርኒያ ግዛት የተገኙት ዶናልድ ትራምፕ ጥፋቱ በቁጥጥር ስር ሊዉል ያልቻለዉ በደካማ የደን ሀብት አስተዳደር የተነሳ ነዉ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ትራምፕ ያጋጠመዉን ከባድ ሰደድ እሳት ተከትሎ እሳቱን በማጥፋት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የነፍስ አን ስራ ለሰሩ ሰባት ግለሰቦች ከፍተኛ የተባለዉን የወታደራዊ የክብር ሽልማትን ሸልመዋል፡፡ሆኖም ግን ዲሞክራቶች የትራምፕ አስተዳደር በካሊፎርኒያ ታሪክ ከባድ የተባለ ሰደድ እሳት ተነስቶ ዝምታን መርጠዋል በሚል ተችተዋቸዋል፡፡

ትራምፕ በአየር ንብረት ለዉጥ ዙርያ የሚያራምዱት ፖሊሲ አሜሪካን የሚጎዳ ነዉ ሲሊ ዲሞክራቲ ተቀናቃኛቸዊ ጆ ባይደን ተናግረዋል፡፡ትራምፕ እ.ኤ.አ በ2015 ከተደረሰበት የፓሪሱ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ስምምነት አሜሪካ ከስምምነቱ እንድትወጣ ማድረጋቸዉ ይታወሳል፡፡

ለትራምፕ ተጨማሪ አራት አመታት በስልጣን እንዲቆዩ መፍቀድ ምን ያህል ሰደድ እሳት እንዲነሳ መፍቀድ ነዉ ሲሉ ባይደን ተናግረዋል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *