መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 6፤2013-በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ለተገደለችው ጥቁር አሜሪካዊት ሴት ቤተሰቦች የ 12 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ካሳ የአሜሪካ መንግስት ሊከፍል ነው

የኬንታኪ ፖሊስ በአደንዛዥ እፅ ዙሪያ ሲያደርግ የነበረውን ቁጥጥር ተከትሎ የ 26 ዓመቷን ብሪኦና ታይለር ፖሊስ በመኖሪያ ቤቷ ሳለች ቢያንስ አምስት ጊዜ ተኩሶ ህወቷ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡

ታይለርን ፖሊስ በስህተት መግደሉን ተከትሎ የጸረ ዘረኝነት ተቃውሞ በአሜሪካ እንዲቀሰቀስ አድርጓል፡፡

በዚህም የተነሳ የኬንታኪ የመንግስት ሃላፊዎች 12 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ካሳ ለብሪኦና ታይለር ቤተሰቦች ለመክፈል ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

የታይለር ወላጅ እናት ታሚካ ፓልመር ወንጀለኞች ለህግ እንዲቀርቡና ፖሊሶች በጥቁር አሜሪካውያኑ ላይ የሚያደርሱት ጥቃት እንዲቆም ማሻሻያ ሊደረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *