መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 6፤2013-በሶማሊያ ከስድስተኛ ፎቅ ላይ አንዲት ሴትን የወረወሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ

በሀገሪቱ መዲና ሞቃዲሾ አራት ግለሰቦች ሀምዲ ሞሀመድ ፋራህ በተባለች ታዳጊ ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ከፈፀሙ በኋላ ከስድስተኛ ፎቅ ላይ ወደ መሬት ይወረውራሉ፡፡

በሞቃዲሾ ጎዳና ላይ ሁኔታውን የተመለከቱ ሰዎች ፍትህ ለመጠየቅ አደባባይ በመውጣት በፀጥታ አካላት የድርጎቱ ፈፃሚዎች እንዲያዙ ጠይቀዋል፡፡

በዚህም መሰረት የሶማሊያ ፖሊስ አራት ከድርጊቱ ጀርባ ነበሩ ያቸውን ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

ሴቶችን ከጥቃት የሚከላከል ረቂቅ ህግ ከፌደራሉ የሶማሊያ ም/ቤት ቢቀርብም መፅደቅ ባለመቻሉ የተነሳ እንዲህ ዓይነት ጥቃቶች በሀገሪቱ ተበራክተዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *