መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 6፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ የሺሃይድ ሱጋ አዲሱ የጃፓን ጠ/ሚ ሆነው ዛሬ ማለዳ ተመረጡ፡፡ ባሳለፍነው ሰኞ ወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው ኮንዘርቫቲቭ ሊበራል ዲሞክራት ለጠ/ሚ ማጨቱን ተከትሎ በዛሬው እለት በህዝብ እንደራሴዎቹ በኩል የጃፓን ጠ/ሚ ተደርገው ተሹመዋል፡፡ በዚህም መሰረት በህመም ከስልጣን የተወገዱትን ሺንዞ አቤን ተክተው ለአንድ ዓመት ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ይመራል፡፡

~ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ የሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን የፃፉት መጽሃፍ ከፋፋይ ነው በሚል ዙሪያ የወንጀል ምርመራ ክስ ሊከፈትባቸው መሆኑ ተሰማ፡፡

~ የአለም የጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒት መርሃ ግብር ለሆነው ኮቫኤክስ ጃፓን 135 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፉን እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡

~ ኤር ኒውዚላንድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ 385 ተጨማሪ የበረራ ሰራተኞቹን ሊቀንስ ስለመሆኑ አስታወቀ፡፡ ኤር ኒውዚላንድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ 37 በመቶ ሰራተኞቹን መቀነሱ ይታወሳል፡፡

~ በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 5 ሚሊዮን በለጠ፡፡ ባለፉት አምስት ቀናት በህንድ በአማካይ በየእለቱ ከ 90ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እየተጠቁ ሲሆን እስካሁን ከ 80 ሺህ በላይ ሰዎች በሀገሪቱ በቫይረሱ የተነሳ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

~ በብራዚል በ 24ሰዓት ውስጥ 1‚113 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተሰማ፡፡ በመላው ብራዚል በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 133‚119 ሲደርስ 4.3 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *