
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ ያካሄዳል።
የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት በላከው መረጃ ምክር
ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ሁለት አጀንዳዎች ላይ ይመክራል።
በቀዳሚነትም የምክር ቤቱን 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ያጸድቋል።
በመቀጠልም የጤና ሚኒስቴር አገራዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች በተመለከተ በሚያቀርበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በመጪው ሰኞ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ የሚያደርግ መሆኑንም ታውቋል።