መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 7፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች


~ ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል አስገዳጅ የነበሩ ህጎች ላይ ማሻሻያ አደረገች።በቀን በቫይረሱ 12ሺ ሰዎች በደቡብ አፍሪካ ይጠቁ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ወደ 2ሺ ዝቅ ብሏል።15 ሺ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል።
~ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሳምንታት ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒት ይቀርባል ሲሉ ቢናገሩም የአሜሪካ ከፍተኛ የጤና ባለስልጣናት ግን ከዚህ ሀሳብ በተቃርኖ ቆመዋል።የትራምፕ ቀጣዩ የምርጫ ተፎካካሪ ጆ ባይደን ትራምፕ ከምርጫው በፊት ክትባት እንዲኖር እናደርጋለን ማለታቸው የማይታመን ሲሉ አጣጥለውታል።
~ በህንድ በ24 ሰዓት ውስጥ የምንግዜውም ከፍተኛ የተባለው 97,894 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ሲመዘገብ ከ1000 በላይ ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል።
~ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጄር ቦርሴናሮ በጤና አመራር ዙርያ ምንም ልምድ የሌላቸዉን ግለሰብ የጤና ሚንስቴር አድርገዉ መሾማቸዉ ተሰማ፡፡ከአራት ወራት በፊት በጊዜያዊነት የተመደቡት ጄነራል ኤድዋርዶ ፓዝዩኤሎ በቋሚነት የጤና ሚንስትር ተደርገዉ ተሹመዋል፡፡
~ በዩጋንዳ ከ200 በላይ ታራሚዎች ማረሚያ ቤት ሰብረዉ ማምለጣቸዉ ተሰማ፡፡ታራሚዎቹ ወታደር በመግደል ማምለጣቸዉ የተነገረ ሲሆን የጸጥታ አካላት ታራሚዎቹ እንዳያመልጡ ሲያደርጉት በነበረዉ ርብርብ ሁለቱ በቁጥጥር ስር ሲዉሉ ሁለት ታራሞዎች መገደላቸዉ ተሰምቷል፡፡
~ የሱዳን መንግስት ለፈንጂ የሚዉል አሙኒየም ናይትሬት አከማችተዉ ነበረ ያላቸዉን 41 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቁ፡፡በአራት ኮንቴነር ዉስጥ የተከማቸ ነበር የተባለ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት በሊባኖስ መዲና ቤሩት ተከማችቶ የነበረ አሙኒየም ናይትሬት ባስከተለዉ ፍንዳታ ከ200 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉ ይታወሳል፡፡
~ ሀሪኬን ሳሊ የተሰኘዉ ከባድ ወጀብና አዉሎ ንፋስ ከግማሽ ሚሊየን በላይ አሜሪካዉያን የሀይል አቅርቦት እንዲቋረጥባቸዉ ማድረጉ ተሰማ፡፡ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ጥፋት እያስከተለ ሲሆን የአራት ወራት አማካይ ዝናብ በአራት ሰዓት ዉስጥ ብቻ በፍሎሪዳ ዉስጥ ተመዝግቧል፡፡
በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *