መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 8፣2013-ነርቭን በሚያጠቃ ንጥረ ነገር የተጠቃው ሩሲያዊ ፖለቲከኛ አርፎበት በነበረው ሆቴል ውስጥ ሣይመረዝ እንዳልቀረ ተነገረ

በሩሲያ የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግስትን በመቃወም የሚታወቀው አሌክሲ ናቫሊን በሰርቢያ ከተማ ቶምስክ አርፎበት በነበረው ሆቴል መኝታ ክፍል በውሃ መጠጫ ጠርሙስ ውስጥ በማድረግ እንዲመረዝ መደረጉን ይፋ ተደርጓል፡፡

ከዚህ ቀደም ኤርፖርቱ ውስጥ ተመርዟል መባሉን የናቫሊን የስራ አጋሮች ተናግረዋል፡፡ በራሺያ መመረዙን ተከትሎ በርሊን ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል፡፡

በሶቬት ጦር አማካይነት ነርቭን እንዲጎዳ ከዓመታት በፊት ተሰርቷል በሚባለው ኖቪቾክ ስለመመረዙ ጀርመን፣ፈረንሳይና ስዊዲን ቢናገሩም ሩሲያ ግን አስተባብላለች፡፡

ይህንን ነርቭ የሚጎዳ ንጥረ ነገር ሀገራት እንዳይጠቀሙ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወቃል፡፡

የአሌክስ ናቫሊን መመረዝ የፑቲን ተቺ በመሆኑ የተነሳ ነው የሚል ክስ እየቀረበ ቢሆንም የሞስኮ አስተዳደር ውንጀላ ውድቅ አድርጓል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *