መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 12፣2013-በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ የቡና፣ ሻይና የቅመማ ቅመም ምርቶች 870 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ፡፡

500 አርሶ አደሮች የቡና ምርታቸውን በቀጥታ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ፈቃድ መውሰዳቸውንም አስታውቋል።በተጠናቀቀው የ2012 በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረበ 270 ሺህ 835 ቶን ቡና 854 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተርና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር ለኢዜአ ገልጸዋል።ከ2011 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀርም በመጠን ከ40 ሺህ ቶን በላይ፤ በገቢ ከ91 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብልጫ እንዳለውም ተናግረዋል።የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት ጀርመን፣ ሳዑዲ አረቢያና አሜሪካ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *