መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 12፣2013-53 ሕገ ወጥ ሽጉጦችና 3860 የሽጉጥ ጥይቶች በወረጃርሶ ወረዳ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ 53 ሕገወጥ ሽጉጦችና 3860 የሽጉጥ ጥይቶች ባለፈው እሁድ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያሉ በጎሃ ቀሬ ከተማ ኬላ ላይ መያዛቸውን የወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር አበባየሁ ገረመው በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩት ግለሰቦችና ሹፌር ያመለጡ በመሆናቸው እነሱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር አበባየሁ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *