መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 12፤2013-የማሊ የቀድሞ የመከላከያ ሚንስትር የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ተደርገዉ ተመረጡ

የማሊ የቀድሞ የመከላከያ ሚንስትር ባህ ኒዳዉ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተደርገዉ ሲሾሙ ከሳምንታት በፊት የተቀነባበረዉን መፈንቅለ መንግስት የመሩት ኮለኔል አሲም ጎታ ምክትላቸዉ በመሆን እንደሚሰሩ ይፋ ተደርጓል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኬታን ከስልጣን ያባረረዉ የጦር መኮንኖች ቡድን ለሲቪል ሀይሎች ስልጣኑን እንዲያስረክብ በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የሚደረገዉ ግፊት አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ከሲቪል የሚወከለዉ መሪ ሀገሪቱ ምርጫ እስከምታካሂድ ለቀጣዮቹ 18 ወራት ማሊን እንዲያስተዳድር መጠየቃቸዉ ይታወሳል፡፡

የማሊ ተቃዋሚዎች ሆነ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ስለ ኒዳዉ ይሁንታ ስለመስጠታቸዉ የተረጋገጠ መረጃ የለም፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *