መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 12፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ ኤር ባስ ከአየር ብክለት ነጻ የሆነ አዉሮፕላን እንደሚያመርት አስታወቀግ፡፡በሀይድሮጀን የሚሰራ የንግድ አዉሮፕላን እ.ኤ.አ በ2035 ለገበያ እንደሚያቀርብ አስታዉቋል፡፡

~ በናይጄሪያ የሚገኙ ታጣቂዎች በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራባዊ ግዛት ዛምፋራ ግዛት አግተዋቸዉ የነበሩ 40 ሰዎችን ከእገታ መልቀቃቸዉ ተሰማ፡፡

~ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ በመላዉ ዓለም ከተመዘገበዉ አምስት ሞት አንዱ በአሜሪካ ስለመሆኑ መረጃዎች አመላከቱ፡፡የተያዘዉ የፈረንጆቹ 2020 ዓመት ሳይጠናቀቅ በወረርሽኙ የተነሳ ህይወታቸዉን በአሜሪካ የሚያጡ ሰዎች ቁጥር 378,000 ሊደርስ እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ግምታቸዉን አስቀምጠዋል፡፡

~ ኢራን ከአሜሪካ ጋር እስረኞችን ለመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላት የሀገሪቱ የዉጪ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ ሞሃመድ ጃቫድ ዛሪፍ ተናገሩ፡፡አሜሪካ በ2015 ከተደረሰበት የቴህራን የኒዉክሌር መርሃ ግብር ስምምነት ካፈገፈገች በኃላ ግንኙነታቸዉ መሻከሩ ይታወቃል፡፡

~ በእስራኤል ማረሚያ ቤቶች ዉስጥ የሚገኙ ፍልስጤማዉያን ሴቶች የወሲብ ጥቃት ሰለባ እየሆኑ እንደሚገኝ የፍልስጤም የደህንነት ኤጀንሲ ይፋ አደረገ፡፡

~ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነዉ ዓርብ ህይወታቸዉን ባጡት የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጊንስበርግ ምትክን በተያዘዉ ሳምንት መጨረሻ የሚያሳዉቁ ሲሆን ከአሜሪካ ምርጫ በፊት በሪፓብሊካኑ አብላጫ የተያዘዉ ሴኔት እንዲያጸድቅላቸዉ አሳስበዋለ፡፡

~ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ በቨርቹል በትላንትናዉ እለት መካሄድ ሲጀምር በኮሮና ቫይረስና በአለም የኢኮኖሚ ዙርያ ያሉ ተግዳሮቶችን እየመከረ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *