መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 13፤2013-በካሜሮን ፖሊስ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ መተኮሱ ተሰማ

የሀገሪቱ የተቃዋሚዎች ፓርቲ CRM መሪዎች እንዳስታወቁት መንግስት ለመቃወም የወጡ ዜጎች በፀጥታ አካላት የጥቃት ሰለባ ውስጥ ወድቀዋል፡፡

የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ክሪስቶፈር ኒዲንግ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ መተኮስ ፣ በቁጥጥር ስር ማዋልና ፣ የሃይል ጥቃት ደግሞም በአስለቃሽ ጋዝ መበተን ተገቢ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

በካሜሩን ታላላቅ ከተሞች ዶአላ ፣ ያውንዴ ፣ ባፋንግና ጋሃም ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡

የተቃውሞ መነሻው እንግሊዝኛ ተናጋሪ በሆኑ የአንግሎፎን ግዛቶች የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪዎቹ ፍራንኮፎን ግዛቶች ጫና ይቁም ዋንኛው ሲሆን በእንግሊዝኛ መማርና መዳኘት ይህ ካልተተገበረ ከካሜሮን የተነጠለች ሀገርን እንፈልጋለን ሲሉ ሰልፈኞች ጠይቀዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የምርጫ ማሻሻያ እንዲደረግ ሰልፈኞች ጠይቀዋል፡፡

ላለፉት 38 ዓመታት የካሜሮን ፕሬዝደንት ፖልቢያ ስልጣኑን እንደተቆጣጠሩ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *