መደበኛ ያልሆነ

ዛሬ መስከረም 19፤2013-በቻይና ተማሪዎቿ እንዲመረዙ አድርጋለች የተባለችው አስተማሪ በሞት እንድትቀጣ ውሳኔ ተላለፈባት

በቻይና ጂአዙዮ ከተማ የመዋዕለ ህጻናት መምህር የሆነቸው ዋንግ ዩን የስራ ባልደረባዋን ለመበቀል ስትል በተማሪዎቹ የቁርስ ሰዓት በሶዲየም ናይትሬት እንዲመረዙ አድርጋለች፡፡

ከስራ ባልደረባዋ ጋር በተማሪዎቹ አያያዝ ጭቅጭቅ ዉስጥ የነበረቸዉ ዋንግ ዩን ተማሪዎቹ ይመገቡበት የነበረው ምግብ ላይ በመጨመር ለከፍተኛ ጉዳት ተማሪዎቹን ዳርጋለች፡፡

በሶዲየም ናይትሬት ዋንግ ሰዎችን ስትመርዝ የመጀመሪያዋ እንዳልሆነ ያስታወቀዉ ፖሊስ ከዚህ ቀደምም ባለቤቷን በምግብ ዉስጥ ብትመርዝም መጠነኛ ጉዳት ብቻ አጋጥሞት አገግሟል፡፡

23 ተማሪዎች በጊዜው እንዲመረዙ ያደረገ ሲሆን የአንድ ተማሪ ህይወት አልፏል፡፡በትላንትናዉ እለት የጂአዙዮ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ ግለሰቧን ጥፋተኛ በማለት በሞት እንድትቀጣ ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡

ሶዲየም ናይትሬት ለስጋ ማከሚያነት የሚያገለግል ሲሆን መጠኑ ከፍ ተደርጎ ሲወሰድ ግን ጎጂ ነው፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *