መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 20፤2013-በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በጆ ባይደን መካከል የመጀመሪያው ዙር ክርክር ተካሄደ

ምሽቱን በሁለቱ እጩዎች መካከል በተካሄደው ክርክር በዋናነት በዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እጩ ፣ በጤና ክብካቤ ዙሪያ እና በኮቪድ-19 ዙሪያ ተከራክረዋል፡፡ በኦሃዮ የተካሄደው ክርክር የፎክስ ኒውስ አዘጋጅ ክሪስ ዋላስ መርቶታል፡፡

በትላንትናው የሁለቱ እጩዎች ክርክር ላይ ትራምፕ በተደጋጋሚ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ንግግርን ሲያቋርጡ ተስተውለዋል፡፡ ኒውዮርክ Times ትራምፕ ለፌደራሉ የገቢዎች መስሪያ ቤት ታክስ በመክፈል ረገድ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያልከፈሉት የታክስ መጠን ከፍተኛ መሆኑን መዘገቡን ተከትሎ ባይደን ትራምፕን በዚሁ ዙሪያ ወርፈዋል፡፡

ባይደን በንግግራቸው እንደገለፁት ትራምፕ አማካይ ገቢ ካለው አስተማሪ ያነሰ ግብርን ይከፍላሉ ይህ ደግሞ ፍትሃዊ አይደለም ብለዋል፡፡ ሁሉም የሚናገረው ነገር ውሽት ነው ከፋፋይ ፣ ፀብ ጫሪ ናቸው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ በቀጣይ ሳምንት በማይክ ፔንስ እና ካማላ ሀሪስ መካከል ክርክር ይደረጋል፡፡

በ90 ደቂቃ ቆይታ 73 አንዳቸው ሌላቸውን አቋርጠዋል፡፡ በውይይታቸው መታዘብ እንደተቻለው ኮሮና ቫይረስ ከ 90ደቂቃው 20ደቂቃውን የያዘ ሲሆን ፤ የኮሮና ቫይረስ የኢኮኖሚ የኢኮኖሚ ተፅዕኖ የማስክ አጠቃቀምና ክትባት ተነስቷል፡፡

ከክርክራቸው 17 ደቂቃን የያዘው ደግሞ ግጭትና የዘር መድልኦ ሲሆን 11 ደቂቃ ስለምርጫው 10 ደቂቃ ደግሞ ስለ አየር ንብረት ለውጥ ተከራክረዋል፡፡ ትራምፕ በክርክር መድረኩ ከጆ ባይደን ያነሰ የተናገሩ ሲሆን ጆ ባይደን 43 ደቂቃ ትራምፕ 38 ደቂቃን ተናግረዋል፡፡

CBS News ከተመልካቾች ሰበሰብኩት ባለው ድምጽ 48 በመቶ ባይደን ፣ 41 በመቶ ደግሞ ትራምፕ በምሽቱ ክርክር እንዲሸነፉ ተናግረዋል፡፡ ክርክሩን ከተመለከቱት መካከል 69 በመቶ የሚሆኑት መበሳጨታቸውን ሲናገሩ 31 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ መዝናናታቸውን ተናግረዋል፡፡

ዲሞክራት የፖለቲካ ተንታኝ የሆነችው ማሪ አኒ ክርክሩ ነፃ ትግል ቢባል ይሻላል ስትል ተናግራለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *