መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 21፤2013-ነርቭን በሚጎዳ ኬሚካል መመረዙ የተነገረው አሌክሲ ናቫሊን ከዚህ ድርጊት ጀርባ ፑቲን አሉበት ሲል ተናገረ

የራሺያ መንግስት ተቃዋሚና የጸረ ሙስና ትግል ዘመቻ አንቂ የሆነዉ አሌክሲ ናቫሊን እንድመረዝ ከመደረጌ ጀርባ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እጅ አለበት ሁኔታዉ ግን አላስፈራኝም ሲል ተናግሯል፡፡

ዴር ስፒገል ለተባለ የጀርመን መጽሄት ሀሳቡን ያጋራዉ ናቫሊን ወደ ሩሲያ እንደሚመለስ እና ያለ ፍርሃት የጀመረዉን ተቃዉሞ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሯል፡፡

ነርቭን በሚያጠቃዉ ኬሜካል መመረዙን ተከትሎ ሁኔታዉን በጊዜዉ ሳስታዉሰዉ ህመም አይሰማህም ግን እንደምትሞት ይታወቅሃል ሲል ተናግሯል፡፡

የፑቲን አስተዳደር በአሌክሲ ናቫሊን መመረዝ ዙሪያ እጄ የለበትም ሲል ማስተባበሉ ይታወሳል፡፡ኖቪቾክ የተባለዉ ነርቭን የሚመርዘዉ ንጥረ ነገር በ1970ዎቹ እና 80ዎች በሶቬቶች አማካይነት የተመረተ ቢሆንም ጥቅም ላይ እንዳይዉል መታገዱ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *