መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 21፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ በዶናልድ ትራምፕ እና በጆ ባይደን መካከል የተደረገዉን ክርክር ተከትሎ የክርክር ደንብ ሊቀየር መሆኑ ተሰማ፡፡በተከራካሪዎቹ መካከል አንዳቸዉ ሌላቸዉን እንዳያቋርጡ የሚጠቀሙበት ማይክራፎን ጣልቃ ለመግባት ሲሞክሩ እንዲቋረጥ ይደረጋል ተብሏል፡፡

~ የኢምሬትስ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ እንዳይበር ተጥሎ የነበረዉ ማዕቀብ መነሳቱ ተሰማ፡፡ማዕቀቡ የተጣለዉ የናይጄሪያ ዜጎች ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እንዳይመጡ መከልከላቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡

~ የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ህገመንግስን በሚጻረር መልኩ ለሶስተኛ ዙር ምርጫ እሳተፋለዉ ማለታቸዉን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ተቃዉሞ ባለፈዉ 2019 ዓመት ከ50 ያላነሱ ሰዎች በጸጥታ አካላት መገደላቸዉን አምኒስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡ምርጫዉ በጥቅምት ወር ይካሄዳል፡፡

~ በግብጽ ከአራት አመት በፊት ሁለት ፖሊሶችን ገድለዋል የተባሉ ስድስት ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ዉሳኔ ተላለፈባቸዉ፡፡

~ ፖፕ ፍራንሲስ ከአሜሪካ የዉጪ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ ማይክ ፖምፒዮ የቀረበላቸዉን የምክክር ቆይታ ዉድቅ አደረጉት፡፡ፖምፒዮ ምክክሩን በህዳር ወር ለሚደረገዉ ምርጫ ከፖፕ ፍራንሲስ ጋር በመገናኘት መጠቀሚያ ሊያደርጉት እንደፈለጉ ተሰምቷል፡፡

~ ኩባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መቀነሱን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ሀቫና በድጋሚ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ማድረጓ ተሰም፡፡

~ ፎርድ ከ700ሺ በላይ የሸጣቸዉን ተሽከርካሪዎች በድጋሚ ወደ ምርት እንዲመጡ ማስጠራቱ ተሰማ፡፡የመጠባበቂያ ካሜራዎቹ የተዛባ ምስሎችን ማሳየታቸዉ በደጋሚ እንዲጠሩ አስገድዷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *