መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 22፤2013-የአውሮጳ ህብረት ቱርክ ጸብ ጫሪ ድርጊቷን የማታቆም ከሆነ ማዕቀብ እንደሚጥል አስታወቀ

ቱርክ ከግሪክ ጋር በኢነርጂ የኃይል ምንጭ እና የባህር ድንበር የተነሳ በመካከላቸዉ ያለው ውዝግብ እንዲካረር ጸብ ጫሪ ድርጊት በማድረግ ረገድ ህብረቱ ቱርክን ወንጅሏል፡፡የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት የሆነችዉ ቮን ደር ሌየን እንደተናገሩት በምስራቃዊ ሜዲትራኒያ ቱርክ የምታደርገዉን የተናጠል እርምጃ እንድታቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ግሪክ እና ቱርክ በይገባኛል እየተወዛገቡበት የሚገኘዉ የባህር ክፍል ከፍተኛ የተፈጥሮ ጋዝና የነዳጅ ሀብት ያለበት ስፍራ ነው፡፡እነዚህ ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ዉዝግብ ይኑርባቸው እንጂ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ኔቶ አባል ናቸዉ፡፡

ቱርክ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገር ለመሆን በረጅም ረድፍ እጩ የተደረገች ቢሆንም በበርካታ ጉዳዮች ጋር ከህብረቱ ጋር በመወዛገብ ትታወቃለች፡፡ህብረቱ ከ2016ቱ የቱርክ መፈንቅለ መንግስት የህግ የበላይነት እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ቱርክን ይተቻል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *