መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 25፤2013-የብስራት አመሻሽ አጫጭር አለም አቀፍ መረጃዎች

~ ቡልጋሪያዊቷ አይነስውሯ ተንባይ ባባቫንጋ ህመም እንደሚገጥማቸው ተናግራ ነበር፡፡ ከ24ዓመት በፊት ህይወቷ ያለፈው ባባቫንጋ የትራምፕ የጆሮ መስማት አቅም እንደሚያጥርና የጭቅላት እጢ እንደሚያጋጥማቸው ተንብያ የነበረ ሲሆን ፤ ትራምፕ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ተከትሎ መረጃው እንደ አዲስ መነጋገሪያ ሁኗል፡፡ ባባ ቫንጋ ስለ 9/11 ጥቃት ፣ ስለ ባራክ ኦባማ መመረጥ ፣ ስለ ሱናሚ አስቀድማ ተናግራለች፡፡

~ በቤላሩስ መዲና ሚኒስክ ከ 100ሺ በላይ ሰልፈኞች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በነሃሴ መጀመሪያ በተካሄደው የሀገሪቱ ምርጫ አሸንፌያለሁ ማለታቸው ተቃዋሚዎቻቸውን አስቆጥቷል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ሃገሪቱን ለ 26ዓመታት መርተዋል፡፡

~ ኒው ካልዶኒዮ ከፈረንሳይ ነፃ ለመሆን የተደረገውን ምርጫ ውድቅ አድርጋለች፡፡

~ እስራኤል በየመን የውስጥ ጉዳይ እየገባች ነው ሲሉ የየመን ጦር ብርጋዴር ጄነራል ያሀያ ሳሪ ተናግረዋል፡፡

~ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ እና ባለቤታቸው ካሪን በድጋሚ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነፃ ሁነዋል፡፡

~ የአለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ለደሃ ሀገራት የብድር ምህረት እንዲያቀርቡ ጥሪ አድርጓል፡፡ በዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የግል ባንኮች እና የኢንቨስትመንት ፈንድ ድጋፍ ዝቅተኛ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *