መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 26፤2013-ከ80 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ሊያሰራጩ የነበሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ !

በምዕራብ ጎጃም ዞን ወምበርማ ሽንዲ ከተማ ከ80 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ሊያሰራጩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

አድራሻቸው ከሰከላ ወረዳ እና ከቡሬ ከተማ የሆኑ 2 ግለሰቦች በወምበርማ ወረዳ በሚገኙ ለንግድ ተቋማትና ለህብረተሰቡ ሀሰተኛ የብር ኖት ሊያሰራጩ ሲሉ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

2ቱ ተጠርጣሪዎች ሀሰተኛ የብር ኖቱን ከባህር ዳር እንዳመጡት ፖሊስ ገልጿል። ብሩን በወምበርማ ወረዳ ሊያሰራጩትም ነበር ተብሏል።

የጸጥታ ሃይል ክትትል እንዳለ ሲያውቁ ወደ ቡሬ ከተማ ተመልሰው በመሄድ ለማሰራጨት ሲሞክሩ ፖሊስ ወደ ቡሬ አብሮ በመሄድና ክትትል በማድረግ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንዳደረጋቸው ተገልጿል።

የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት በክትትል እና ስምሪት ላይ ለነበሩት የፖሊስ አባላቱ ምስጋና አቅርቧል።

ምንጭ፦ የወምበርማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *