መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 26፤2013-የላይቤሪያዉ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ገንዘብ እንዲሰጣቸዉ የጠየቁ የሀገሪቱ ታዳጊ ወጣቶችን ተችተዋል፡፡

በ18 ዓመቴ በረንዳ ላይ እየተኛዉ ራሴን ለመለወጥ እተጋ ነበር፤የሀገሪቱ የ18 እና የ19 ዓመት ወጣቶች በራሳችሁ እግር መቆምን መልመድ አለባችሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ዊሃ ወደ ስልጣን ሲመጡ በስራ እድል ፈጠራ በኩል የገቡትን ቃል መፈጸም አልቻሉም በሚል እየተተቹ ይገኛል፡፡

የቀድሞ የእግር ኳስ ኮከብ የ54 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዊሃ ደጋፊዎቻቸዉ በጹሁፍ መልዕክት ሊረዳን አልቻለም በሚል ስድብ እያስተናገዱ ይገኛል፡፡ጆርጅ ዊሃ እንደተናገሩት ከሚላክልኝ 1000 የጹሁፍ መልዕከት 999ኙ ስድብ ነዉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ክብረ ነክ በሆነ መልኩ ለሚቀጥል ዘለፋ ምንም ዓይነት ድጋፍ በግላቸዉ እንደማያደርጉ ዊሃ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *