መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 26፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር አለም አቀፍ መረጃዎች

~ ካናዳ በቱርክ ላይ የጦር መሳሪያ ግዢ ማዕቀብ እንደምትጥል አስታወቀች፡፡የቱርክ መንግስት በአዘርባጅን አርሜንያ ዉጊያ አዘርባጅንን በመደገፍ ተሰልፏል፡፡ካናዳ ሰራሽ የጦር መሳሪያዎችን በዚህ ዓይነቱ ጦርነት መጠቀም አግባብ አይደለም ሲሉ የካናዳ የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ፊሊፕ ተናግረዋል፡፡

~ ሳዑዲ አረቢያ እና እስራኤል የዲፕሎማሲ ግንኙነት ባይኖራቸዉም የሳኡዲ አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን በተደጋጋሚ ወደ እስራኤል መዲና ቴላቪቭ ጉብኝት ያደርጉ እንደነበር አል ማዲያን የተባለ የሊባኖስ ቴሌቪዥን የእስራኤል መንግስት ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

~ በአልጄሪያ መዲና አልጀርስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኖች በሀገሪቱ አደባባይ በመዉጣት የፖለቲካ ለዉጥ እንዲመጣ ጥያቄያቸዉን አሰምተዋል፡፡

~ በይርግዚስታን ባሳለፍነዉ እሁድ የተካሄደዉን ምርጫ ተከትሎ በዉጤቱ ያልተደሰቱ ተቃዎሚዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል ከ120 ያላነሱ ሰዎች ጉዳት እንዳጋጠማቸዉ ተነግሯል፡፡

~ ከስድስት ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ ሱዳን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ እንዲዘጉ ዉሳኔ አሳልፋባቸዉ የነበሩትን ትምህርት ቤቶች በትላንትናዉ እለት ከፈተች፡፡

~ በሌሴቶ የቲዉተር ተጠቃሚ ሆነዉ ከ100 በላይ ተከታይ ያሉቸዉ ሰዎች የኢንተርኔት የመረጃ ስርጭት በሚል መመዝገብ እንዳለባቸዉ የሚያስገድድ ረቂቅ ህግ ቀርቧል፡፡

~ በሆንግ ኮንግ 102 ካራት ነጭ ዳይመንድ በ15.7 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ተሸጠ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *