መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 27፤2013-ሚሼል ኦባማ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዘረኛ ናቸው ሲሉ ተናገሩ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ ዘረኛ ፣ ከፋፋይ ፣ አስቀያሚ የሆነ የሴራ መሪ ነው ስትል ተናግራለች፡፡

አራት ሳምንታት ብቻ በቀሩት በአሜሪካ ምርጫ ትራምፕ በድጋሚ ሊመረጥ አይገባም ሲሉ ሚሼል ኦባማ ተናግረዋል፡፡

በጥቁር አሜሪካዊያን ዙሪያ ተገቢ ያልሆነ ፍርሃትን ለመፍጠር ትራምፕና የሪፐብሊካን ፓርቲ አጋሮቻቸው ይሰራሉ ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

24ደቂቃ በፈጀው የሚሼል ኦባማ የቪዲዮ መልዕክት ትራምፕ የኮሮና ቫይረስ ቀውስን የመመከት አስተዳደር አለመወጣታቸውን ገልፀው አሜሪካውያን በኢራቅ ፣ አፍጋኒስታን ፣ ቬትናም እና ኮርያ ጦርነት በድምሩ ከተገደሉት በላይ ኮሮና ህይወታቸውን አጥተዋል ለዚህ የትራምፕ ደካማ ምላሽ ነው ብለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *