መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 27፤2013-ሩሲያ በአዘርባጃን እና አርሜንያ መካከል ወደ ግጭት የተገባበት የድንበር ስፍራ የጁሃዲስቶች የጥቃት መዳረሻ ሊሆን እንደሚችል አስታወቀች

የናጎርኖ ካራባክህ ስፍራ ጥቃት ለመሰንዘር የሚፈልጉ ሃይሎች ወደ ሩሲያ ለመግባት በር ሊያገኙ ይችላሉ ስትል ራሺያ አስጠንቅቃለች፡፡

የክርሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቪ እና የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ግጭቱ በሚቆምበት ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከሀገራቱ ጋር ድንበር የምትጋራው ኢራን ግጭቱ ስጋት እንደፈጠረባት በመግለጽ ያነሱትን ብረት ሀገራቱ እንዲያስቀምጡ ፣ ለቀጠናው ሰላም ብቻ እንደሚበጅ የኢራን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ ተናግረዋል፡፡

በአርሜንያ እና አዘርባጃን መካከል የተጀመረው የድንበር ግጭት የአዛሪን የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ በብቸኝነት ለማስተላለፍ ከመነጨ የይገባኛል ጥያቄ ነው፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል በተፈጠረውና አስር ቀናት ባስቆየረው ግጭት ከ 270 በላ ሰዎች ተገድለዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *