መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 27፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ የ‹‹ብላክ ሆል›› መገኛ በምርምራቸው ያገኙ ሶስት ሣይንቲስቶች 2020 የኖቤል የፊዚክስ አሸናፊ ሆኑ፡፡ ብሪታናዊው ሮጀር ፔንሮዝ ፣ ጀርመናዊ ጌንዝል ፣ አንድሬ ጊህዝ ሽልማቱን ይጋራሉ፡፡

~ የይርጊዚስታን ጠ/ሚ ኩባታቢ ቦሮኖቪ በሀገሪቱ ውስጥ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ስልጣን መልቀቃቸው ተሰማ፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሳይድር ዛፓሮቪ ከእስር የተለቀቁ ሲሆን ቀጣይ ጠ/ሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

~ በሶሪያ አል ባብ በአውቶቡስ ማቆሚያ ስፍራ በከባድ ተሸከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ በትላንትናው እለት 18 ሰዎች ሲገደሉ ቢያንስ 74 ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡

~ ፌስቡክና ቲውተር ትራምፕ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ያስተላለፉት መልዕክት አሳሳች ነው በሚል እንዲወገድ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡

~ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ እና የዲሞክራቶች እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሴናተር ካማላ ሃሪስ በዛሬው እለት ክርክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

~ የፕሬዝዳንት ፑቲን አስተዳደርን በመተቸት የሚታወቀው አሌክሲ ናቫሊ ከደሙ ላይ በተወሰደ ናሙና መሰረት ነርቭን በሚያጠቃ ኖቪቾክ መጠቃቱን የዓለም አቀፍ የኬሚካል የጦር መሳሪያ ተቋም ይፋ አደረገ፡፡ በሶቬቶች የተሰራው ይህ የሚመርዝ ኬሚካል ጥቅም ላይ እንዳይውል መከልከሉ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *