መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 29፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች

~ በደቡብ ኮርያ ባለ 33 ወለል ህንጻ ላይ የተቀሰቀሰዉ እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ፡፡እሳቱን ለመቆጣጠር 13 ሰዓታት የፈጀ ሲሆን ከ80 በላይ ሰዎች ጉዳት አጋጥሟቸዉ ወደ ሆስፒታል አቅንተዋል፡፡

~ የአለም የጤና ድርጅት በትላንትናዉ እለት ከምንግዜዉም ከፍተኛ የተባለዉ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በአንድ ቀን መመዝገቡን ይፋ አደረገ፡፡በ24 ሰዓት ዉስጥ ብቻ 338,779 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ ከዚህ ዉስጥ በአዉርጳ 96,996 ተጠቂዎእ ተመዝግቧል፡፡

~ በአልጄሪያ የ19 ዓመቷ ወጣት ቻአይማ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ከደረሰባት በኃላ በህይወት እያለች በእሳት ተቃጥላ ህይወቷ እንዲያልፍ መደረጉ በሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃዉሞ አስነሳ፡፡በድርጊቱ ፈጻሚ ላይ የሞት ብይን እንዲሰጥ ዜጎች አደባባይ በመዉጣት ቁጣቸዉን ገልጸዋል፡፡

~ ሰሜን ኮርያ በነገዉ እለት የሀገሪቱ የሰራተኞች ፓርቲ የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ታላቅ ወታደራዊ ትርዒት ታካሂዳለች፡፡በመዲናዋ ፒዮንግ ያንድ ከሚኖረዉ ደማቅ ወታደራዊ ትርዒት በተጨማሪ ሀገሪቱ የባልስቲክ ሚሳኤል ልታስወነጭፍ ትችላለች፡፡

~ በአዘርባጃንና አርሜንያ መካከል የተቀሰቀሰዉ የድንበር ግጭት እንዲያበቃ የተደረገዉ የዲፕሎማሲ ሂደት ዉጤት አለማስገኘቱ ተነገረ፡፡

~ በጂሃዲስቶች ታግተዉ የነበሩ የማሊ ፖለቲከኛ እና የፈረንሳይ ዜጋ የረድዔት ተግባር ሰራተኛ ከእገታ ተለቀቁ፡፡

~ በኢንዶኔዥያ ኢንቨስትመንትን ለማነቃቃት የወጣዉ አዲስ ህግ የስራ እድል የሚዘጋ ነዉ ያሉ ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡በመዲናዋ ጃካርታ ህጉ ተግባራዊ መሆን የለበትም ያሉ ሰልፈኞችን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝና ዉሃ ተጠቅሟል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *